Publications

Creating awareness

image description

ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡-

  1. የከተማዋን ሁለንተናዊ ጽዳት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ሥራዎችን ያከናውናል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤
  2. የከተማው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብ፣ አጓጓዝና አወጋገድ የህዝብ ጤናን በማይጎዳና የአካባቢ ብክለትን በማይፈጥር መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤
  3. በህብረተሰቡ ዘንድ የአመለካከትና የባህሪይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ የትምህርትና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በየደረጃው ያከናውናል፤ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችንም ይሰጣል፤ እንዲሰጥም ያስተባብራል፤
  4. የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስራዎችን ለመተግበር በከተማ ደረጃ የወጡና የፀደቁ ፖሊሲና ህጎች በየደረጃው እንዲፈፀሙ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  5. የህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና የግል የጽዳት ድርጅቶች በከተማው የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስራዎች የሚሳተፉበትን አማራጮች በማጥናት እንዲተገበር ያደርጋል፤
  6. ደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ የሚቀንስበትንና የሚለይበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ የደረቅ ቆሻሻ የመልሶ መጠቀምና ማስወገድ ስራዎች በአግባቡ መፈፀማቸውንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  7. ለአገልግሎቱ የሚወጣው ወጪ በተገልጋዮች የሚሸፈንበትን የታሪፍና የክፍያ ስርዓት አጥንቶ ያቀርባል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
  8. የግል ባለሀብቶችና የግል ጽዳት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ይገመግማል፤ የብቃት ማረጋገጫ፤ የምስክር ወረቅትና የስራ ፍቃድ ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤
  9. የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከላትንና ስፍራዎችን ያስተዳድራል፤ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን የማስወገጃ ቦታው በህዝብ ጤና እና በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ በማያስከትል መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  10. የመልሶ መጠቀሚያ ማዕከላትና የማስወገጃ ቦታ የደረቅ ቆሻሻ በክብደት ሚዛን የሚመዘንበትንና ትክክለኛ መጠኑ የሚታወቅበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ መረጃዎችን መዝግቦ ይይዛል፤ ያሰራጫል፤ እንዲሁም የከተማዋን የደረቅ ቆሻሻ አጠቃላይ ሁኔታ ከመረጃው ተነስቶ ማስተካከያ የሚደረግባቸውን መረጃዎች በማደራጀት ለወሳኝ አካል ያቀርባል፤
  11. የደረቅ ቆሻሻ ጊዜአዊ ማስቀመጫ ቦታዎችን በከተማው የተለያዩ አቅጣጫዎች በማጥናት እንዲገነቡና ጥቅም ሊይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
  12. የመልሶ መጠቀምና የቀልዝ (የብስባሽ ማዳበሪያ) ማዕከላትን በማስፋፋት ደረቅ ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውልበትን፣ ጠቃሚ ውጤት የሚያስገኝበትን የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች በማጥናት እንዲተገበሩ ያደርጋል፤ ውጤታቸውንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  13. መልሶ መጠቀሚያ ማዕከላትና ማስወገጃ ቦታ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ በማጥናት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ይተገብራል፤
  14. የአዲስ ሳኒተሪ ላንድፊል እና ከቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ቦታ መረጣ፣ የጥናትና የማልማት ስራዎችን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
  15. የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም ማሽነሪዎችን ያሰማራል፣ያስተዳድራል፡፡
  16. ዓላማውን ከግብ ሊያደርሱ የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤