Events

In Public Consultations and Town Halls

image description
Start Date icon
End Date icon
Location የካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን

value="

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ መጪውን የትንሳኤና የስቅለት በዓላትን ምክንያት በማድረግ በነገው እለት ሀሙስ ሚያዚያ 01/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ በመዲናዋ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሰፊ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር የሚያካሂድ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ደግሞ በድምቀት እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ይህ የፅዳት ንቅናቄ በዋነኝነት የክርስትና እምነት ተከታዮች የስቅለት በዓልን አስመልክቶ የፀሎትና ስግደት ስነስርዓት በሚያከናውኑባቸው አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ትኩረቱን አድርጎ የሚከናወን ይሆናል።

የንቅናቄ መርሀግብሩ ዋና ዓላማም የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲያከብሩ ለማስቻልና በከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ያለውን የወንድማማችነትና የእህትማማችነት መንፈስ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሆነ ተመላክቷል።

በነገው እለት በሚከናወነው በዚህ መጠነ ሰፊ የፅዳት ንቅናቄ ስራ ላይ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የኃይማኖት አባቶች፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚሳተፉ ይሆናል።

ኤጀንሲው መላው የከተማዋ ነዋሪዎችም ከበአሉ ጋር ተያይዞ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻና የእርድ ተረፈ ምርት በአግባቡ በመያዝ እና የአካባቢያቸውን ንፅህና በመጠበቅና  በሚከናወነው የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበዓሉ ድምቀት እንዲሆኑ ጥሪውን አቅርቧል።

"

  • icon 9:30am - 1:00pm
  • የካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን

Related Events

image description
Public Consultations and Town Halls

  • የካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
More Details