“Care should be taken to ensur...

image description
- In pulice partspation    0

“Care should be taken to ensure that animal by-products do not contaminate the environment during slaughter,” said Mr. Sadiq Shikur.

ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት በሚከናወን እርድ ተረፈ ምርቶች አካባቢን እንዳይበክሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡

የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳዲቅ ሽኩር በዓሉን ምክንያት አድርገው በሰጡት መግለጫ ህብረተሰቡ በበዓላት ወቅት የእርድ ተረፈ ምርቶች የአካባቢውን ጽዳት እንዳያበላሹ የሚመነጨውንም ደረቅ ቆሻሻ ለጽዳት ሰራተኞች በመስጠትና ቆሻሻን በተገቢው መንገድ ማስወገድ ይጠበቃል፡፡

አቶ ሳዲቅ እንደገለጹት ህብረተሰቡ ቆሻሻን ከመጣል ይልቅ ለጽዳት ሰራተኞች በሚመች መልኩ በማስቀመጥ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡ በእርድ ወቅት የእንስሳት ተረፈ ምርቶች በአግባቡ ተለይተው ለጽዳት ሰራተኞች ካልቀረቡ በሚጥሉበት አካባቢ ላይ በመበስበስ ከፍተኛ የሆነ ሽታን ይፈጥራል፡፡ ይህም በህብረተሰቡ ጤና ላይ ችግር ያመጣል ያሉ ሲሆን በእርድ ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ከተቻለ በተለያዩ ቆሻሻዎች ምክንያት ከሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች እራስንና ቤተሰብንም መጠበቅ ይቻላል ብለዋል፡፡

ከመደበኛው ስራ ጎን ለጎን የበዓላትንና የአደባባይ ሁነትን ታሳቢ ያደረጉ የጽዳት ስራዎች ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰራ ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የእንስሳት እርድም ሆነ በአደባባዮች ላይ የሚመነጩ ደረቅ ቆሻሻዎች አካባቢን የመበከል ዕድላቸው ስፊ ስለሆነ በየአካባቢው ትምህርት በመስጠት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ከህብረተሰቡ መኖሪያ ቤት የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በህብረት ሽርክና ጽዳት ማህበራት እንዲሁም ከሆቴሎች እና ከተቋማት የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ ደግሞ በግል ጽዳት ድርጅቶች እተሰበሰበ እንደሚገኝ ጠቁመው ደረቅ ቆሻሻን የሚሰበስቡ ጽዳት ድርጅቶችና ማህበራት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ ዕርድን በህገ ወጥ መንገድ በየቦታው ከማከናወን ይልቅ በቄራዎች ድርጅት በማድረግ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ሊሳተፍ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህብረተሰቡ ከዕርድ በተጨማሪ ተረፈ ምግብን ጨምሮ ሌሎች ደረቅ ቆሻሻዎችን ለይቶ ማስቀመጥ ይኖርበታል ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ ደረቅ ቆሻሻን መቅበርና ማቃጠል የራሱ የሆነ ችግር ያለው በመሆኑ ህብረተሰቡ ከዚህ ድርጊት ተቆጥቦ ደረቅ ቆሻሻን በአይነት ለይቶ በማስቀመጥ የከተማዋን ጽዳት ለመጠበቅ በሚደረገውን ዘርፈ ብዙ ርብርብ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments