አገልግሎት የሰጡ የፕላስቲክ ቁሶችን በአግባቡ በ...

image description
- In pulice partspation    0

አገልግሎት የሰጡ የፕላስቲክ ቁሶችን በአግባቡ በማስወገድ፣ አካባቢያችንን ከብክለትና ከጎርፍ አደጋ ስጋት እንከላከል!

አገልግሎት የሰጡ የፕላስቲክ ቁሶችን በአግባቡ በማስወገድ፣ አካባቢያችንን ከብክለትና ከጎርፍ አደጋ ስጋት እንከላከል!

በየዓመቱ የበልግ እና የክረምት ዝናብን ተከትሎ በመዲናችን ከሚስተዋሉ ክስተቶች መካከል የጎርፍ አደጋ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእርግጥ ዝናብ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት አካል በመሆኑ ማስቆም አይቻልም፡፡ ከዝናብ መጠንና ስርጭት ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለው የጎርፍ አደጋም፣ በተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ዑደት ውስጥ የሚታይ ክስተት በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ለመከላከል አዳጋች ይሆናል፡፡

ይሁን እንጂ በከተማችን ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የጎርፍ አደጋ ከፍ ብሎ ከተጠቀሰው መሠረተ-ሃሳብ በተቃራኒ፣ እኛው ራሳችን በምንፈጥረው ያልተገባ ድርጊት ሳቢያ የሚፈጠር ሰው ሰራሽ ችግር ስለመሆኑ የተለያዩ ማሳያዎችን በማንሳት ማሳየት ይቻላል፡፡

ለአካባቢ ብክለትም ሆነ ለጎርፍ አደጋ መከሰት አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደሩ ከሚገኙ አማጭ ምክንያቶች መካከል በዘፈቀደና በግዴለሽነት፣ በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮችና ድልድዮች አካባቢ የምንጥላቸው ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ቁሶች ይጠቀሳሉ፡፡

በተለይም እሽግ ውሃ የሚቀርብባቸው የፕላስቲክ ኮዳዎች እና የእቃ መያዣ ፌስታሎች በቀላሉ የማይበሰብሱናባሉበት ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ በመሆኑ፤ የድሬኔጅ መስመሮች እንዲደፈኑ እና የዝናብ ውሃ ወደ መንገድ ገንፍሎ ለጉዳት እንዲዳርግና  የከተማችን ገፅታ እንዲበላሽ ከማድረጋቸውም በላይ፣ ክቡር በሆነው የሰው ልጅ አካልና ህይወት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደርጋሉ፡፡

ስለሆነም የፕላስቲክ ቁሶችን ከተጠቀምን በኋላ በኃላፊነትና በአግባቡ በማስወገድ፤ አካባቢያችንን ከብክለት፣ ህይወትና ንብረታችንን ከጎርፍ አደጋ ስጋት እንከላከል!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments