አዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

image description
- In Uncategorized    0

አዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡

የሀገራችንና የአፍሪካ ህብረት ማዕከል የሆነችውን አዲስ አበባ ከእድገቷና ከስልጣኔዋ ጋር የሚመጣጠን በሁሉም አቅጣጫ የጸዳች ከተማ ለማድረግ መንግስት የሚሰጠው ትኩረት ከፍተኛ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ሳይንሳዊ አሰራርን እየተከተለ ከተማችን በምትፈልገው የጽዳት ደረጃ እድትደርስ እየሰራ ይገኛል፡፡

በከተማችን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያላቸው እንቅስቃሲዎች ከመካሄዱ ጎን ለጎን የከተማዋ ስፋትና የነዋሪው ብዛት እየጨመረ፣ የሚካሄደው መሠረት ልማት ግንባታ፣ ዕድገቱን ተከትሎ የነዋሪው የቀንና የወር ገቢ እያደገ በመምጣቱ በዚያው ልክ ለፍጆታና ለአገልግሎት የሚውሉ ምርቶች እና ሸቀጦች እንዲሁም በከተማዋ ከፍተኛ እና ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መምጣታቸው የሚመነጨውም ደረቅ ቆሻሻ ያን ያህል እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

ይህን የሚመነጭ ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ለመቆጣጠር የሕብረተሰቡን ክፍል በተለያየ ደረጃ ማለትም እድርን፣ የሀይማኖት ተቋማትን፣ የግልና የመንግስት ተቋማትን፣ የትምህርት ተቋማትን፣ የጽጥታ አካለትን፣ ከታችኛው እስከ ላይኛው ያሉ አመራሮችን፣ ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎችን፣ የከተማችን አንቱታን ያተረፉ ሽማግሌዎችን፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ አትሌቶችን፣ የስፖርት ቤተሰቦችን፣ የጽዳት አምባሳድር ሆነው የተመረጡ ሰዎች እና የሚዲያ ተቋማትን በጽዳት ስራው ላይ በማሳተፍ ላይ እንገኛለን፡፡ እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ የጀመርነውን የግንዛቤ አሰጣጥ ስልቶቻችንን አጠናክረን በመቀጠል በሕብረተሰቡ ዘንድ ስር ነቀል የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ስንችል በመሆኑ በትግል ላይ ነን፡፡

በተመሳሳይም የከተማችንን ጽዳት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የቤት ለቤትና የተቋማት የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ አገልግሎቱን በስታንዳርዱ መሰረት በመስጠት ላይ እተረባረብን እንገኛለን፡፡ አገልግሎቱን ያላገኘ ሕብረተሰብ፣ በዘርፉ ብልሹ አሰራሮች ሲተገበር እና በሕገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ ተዝረክርኮ ቢታይ በነጻ የስልክ መስመር 6199 ላይ እንዲጠቁሙን በማድረግ ለጥቆማዎቹ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ላይ ነን፡፡

በተለይ ጽዳት የአንድ ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ ትልቁ መገለጫ ከመሆኑም በላይ የስልጣኔ ምልክት ነው፡፡ ስለሆነም በአሰራሩና በአደረጃጀቱ እንዲሁም በሰለጠነ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በተለያዩ ግብዓቶች እየተደገፈ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደረቅ ቆሻሻ ወደ ሀብት ከመቀየር አኳያ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተገኘበት እንዲሁም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድሎችን መፍጠር የተቻለበትና በአጠቃላይ እንቅስቃሴዎቻችን በጽዳት ተደራሽነት ረገድ መሰረታዊ ለውጦች የታዩበት ቢሆንም አሁንም ማህበረሰቡን ባለቤት በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ይታመናል፡፡

በመሆኑም ከተማችንን ጽዱ፣ ለኑሮና ለስራ እንዲሁም ለቱሪዝም መስህብ ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸውን ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሁላችንም ኃላፊነት ስለሆነ ለዚህ መረጋገጥ በጋራ እንረባረብ እላለሁ፡፡ በመጨረሻም የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲን ድረ-ገጽ በመጠቀም አጠቃላይ መስሪያ ቤቱን ስለሚመለከቱ ጉዳዮች ገንቢ አስተያየታችሁን እንዲትሰጡን እየጋበዝኩኝ ድረ-ገጻችንን ስለጎበኙ እናመሰግናለን።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments